ድግምት "ሲሕር" ምንድነው?



ሺፋዕ የመንፈሳዊ ህክምና እና የምክር አገልግሎት

https://www.facebook.com/nosihr

ሺፋዕ የመንፈሳዊ ህክምና እና የምክር አገልግሎት

https://www.facebook.com/nosihr

ድግምት "ሲሕር" ምንድነው?

ሲሕር” (ድግምት) በዓረብኛ ቋንቋ ስውር የሆነና ምክንያቱ ያልታወቀ ነገር ማለት ሲሆን ሸሪዓዊ ትርጉሙ ደግሞ፤ ልብን ወይም አካልን የሚያሳምምና እስከ መግደል ድረስ ተፅዕኖ የሚያሳድር፣ ባልና ሚስትን የሚለያይና በሰላማዊ ህይወት ላይ እንከን የሚፈጥር የደጋሚዎች ልፍለፋ፣ ትብተባና መተፋፋት ነው። ለመከሰቱ የአላህ ፍቃድ ከሌለ በስተቀር ድግምት ተፅዕኖ ሊያሳድር አይችልም። ድግምት ኩፍር ሲሆን ድግምተኛም በአላህ የካደ ካፊር ነውና በመጪው አለም ምንም ዕጣ ፈንታ የለውም፡፡ ከድግምት እና ከድግምት ሰዎች በአላህ እንድንጠበቅ አላህ አዞናል።

አላህ እንዲህ ብሏል፦

قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ (1) مِنْ شَرِّ مَا خَلَقَ (2) وَمِنْ شَرِّ غَاسِقٍ إِذَا وَقَبَ (3) وَمِنْ شَرِّ النَّفَّاثَاتِ فِي الْعُقَدِ (4) وَمِنْ شَرِّ حَاسِدٍ إِذَا حَسَدَ

በል «በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ፡፡ ከፈጠረው ፍጡር ሁሉ ክፋት፡፡ ከሌሊትም ክፋት ባጨለመ ጊዜ፤በተቋጠሩ (ክሮች) ላይ ተፊዎች ከኾኑት (ደጋሚ) ሴቶችም ክፋት፡፡ከምቀኛም ክፋት በተመቀኘ ጊዜ፤ (እጠበቃለሁ በል)፡፡» (አል ፈለቅ 1-5)

የድግምት አይነቶች

 
ሁለት ዋና ዋና የድግምት አይነቶች ይገኛሉ፤

1.
ሲህሩ አል-ተኸዩል
2. ሲህሩ አል-ሀቂቃህ

በአላህ ፍቃድ በቀጣይ ሁለቱንም ክፍሎች በዝርዝር ለመመልከት እንሞክራለን!

ፔጁን ላይክ ለማድረግ፡-
https://www.facebook.com/nosihr

ሼር በማድረግ ሙስሊሙን ዑማ በብዛት እየጎዳ ያለውን የሲህር በሽታ ለመከላከል የበኩሎን አስተዋፅዖ ያበርክቱ!


Comments