ሩቃ
ሀ. ትርጉሙ፦
“ሩቃ” ሩቅያ ለተሰኘው የዓረብኛ ነጠላ ቃል ብዜት ሲሆን ሩቅያ ማለት በሽተኛን ለመፈወስ የሚነበነቡ
ከቁርአንም ይሁን ከሀዲስ ጥቅሶች ማለት ነው፡፡
ለ. ሸሪዓዊ ብይኑ፦
የተፈቀደ ነው፡፡ ከማስረጃዎች ውስጥ ዓውፍ ኢብኑ ማሊክ እንዳሉት
“በድንቁርና ዘመን በሽተኛ ላይ እናነብ ነበርና የአላህ መልዕክተኛ
ሆይ! እንዴት ያዩታል? ብለን ጠየቅናቸው፡፡ እሳቸውም ምታነቡትን
ግለፁልኝ፤ ማጋራት የሌለበት እስከሆነ ድረስ በሽተኛ ላይ ማንበብ ችግር የለውም አሉ” ሙስሊም ዘግበውታል
አነስ ኢብኑ ማሊክ እንዲህ ብለዋል “የአላህ መልዕክተኛ ﷺ
ለቡዳ በሽታ፣ ለመነደፍና ቁስለት
ሩቃ ማድረግ ፈቅደዋል” ሙስሊም ዘግበውታል
ጃቢር ኢብኑ ዐበደላህ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ
እንዲህ ብለዋል “ወንድሙን (ከህመሙ ለመፈወስ በመቅራት) መጥቀም የቻለ ያድርግ››
ሙስሊም ዘግበውታል
ከአዒሻ እንደተዘገበው የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ከኛ ውሰጥ አንዱ ሲታመም በቀኝ እጃቸው እየዳበሱት እንዲህ ይሉ ነበር “የሰዎች ጌታ ሆይ!
ጉዳትን አስወግድ፤ፈውሰው አንተ ፈዋሸ ነህ ከአንተ ሌላ ፈዋሽ የለም ህመምን በማያስቀር ፈውስ ፈውሰው” ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
መ. መስፈርቶቹ፦
ሩቃ የሚፈቀደው ሶስት መስፈርቶች ሲሟሉ ነው:: እነሱም፡-
አንደኛ፡- ከአላህ ፈቃድ ውጭ ያድናል
በሚል ሊታመን አይገባም፡፡ ከአላህ ፈቃድ ውጭ እንደሚጠቅም ማመን ሽርክ በመሆኑ የተከለከለ ነው፡፡
ሁለተኛ፡- ሸሪዓን የሚጋጭ መሆን የለበትም፡፡ ለምሳሌ ከአላህ ሌላ መለመን ወይም ከጭንቅ እንዲገላግል ጋኔንን መጥራት የመሳሰሉት ከታከሉበት ሽርክ በመሆኑ
ክልክል ይሆናል፡፡
ሶስተኛ፡-
ግልፅ የሆነ ትርጉም ያለው መሆን
አለበት፡፡ ትርጉም የሌለው አተታ ከሆነ አይፈቀድም፡፡
ኢማም ማሊክ
እንዲህ በሚል ተጠየቁ “የታመመ ሰው ላይ መቅራት ይቻላልን?
እሳቸውም እንዲህ በማለት መለሱ “በመልካም ቃላቶች ከሆነ ችግር የለውም፡፡”
ሠ. ክልክል የሆነ ሩቅያ፡-
ከላይ የተጠቀሱ መሰፈርቶች ያልተሟሉበት ሩቅያ በመሉ ክልክል ነው::
ለምሳሌ አንባቢው ወይም የሚነበብለት ሰው ሩቅያ ራሱን ችሎ ፈውስ ነው በሚል የሚያምን ከሆነ ወይም ሩቅያው የሽርክ የቢድዓ የመሳሰሉ
ቃላቶችን ያቀፈ ከሆነ ወይም ደግሞ ትርጉም በሌለው አተታ ከሆነ አይፈቀድም፡፡
ውድ አንባቢ ሆይ! ቁርአን ሁሉም መታከሚያ እንደሆነ ጥርጥር የለውም እንደዚሁም ለአማኞች መድሃኒት ነው፡፡ አላህ እንዳለው፡-
ﮋ ﮤ ﮥ ﮦ
ﮧ ﮨ ﮩ ﮪ ﮫﮬ
ﮭ ﮮ ﮯ
ﮰ ﮱ ﯓ ﮊ
الإسراء: 82
“ከቁርአንም ለምእመናን መድሃኒትና እዝነት የኾነን እናወርዳለን፣ በዳዩችንም ኪሳራን እንጂ ሌላ
አይጨምርላቸውም”
(አል ኢስራእ 82)
በሌላም አንቀፅ እንዲህ ብሏል
وَلَوْ جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا
أَعْجَمِيًّا لَّقَالُوا لَوْلَا فُصِّلَتْ آيَاتُهُۖ
أَأَعْجَمِيٌّ وَعَرَبِيٌّۗ قُلْ
هُوَ لِلَّذِينَ آمَنُوا هُدًى وَشِفَاءٌۖ
وَالَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ فِي آذَانِهِمْ وَقْرٌ وَهُوَ عَلَيْهِمْ عَمًىۚ أُولَٰئِكَ يُنَادَوْنَ مِن مَّكَانٍ
بَعِيدٍ [41:44]
“በአጀምኛ የኾነ ቁርኣን ባደረግነው ኖሮ አንቀጾቹ «(በምናውቀው ቋንቋ) አይብራሩም ኖሯልን? (ቁርኣኑ) አጀምኛና (መልክተኛው)
ዐረባዊ ይኾናልን?» ባሉ ነበር እርሱ ለእነዚያ ለአመኑት መምሪያና መፈወሻ ነው፡፡ እነዚያም የማያምኑት በጆሮዎቻቸው
ውስጥ ድንቁርና ነው፡፡ (አይሰሙትም)፡፡ እነርሱም በእነርሱ ላይ እውርነት ነው፡፡ እነዚያ ከሩቅ ስፍራ እንደሚጠሩ ናቸው፡፡”
(ፉሲለት 44)
Comments
Post a Comment