1. ሲህሩ አል-ተኸዩል


ሺፋዕ የመንፈሳዊ ህክምና እና የምክር አገልግሎት
https://www.facebook.com/nosihr

የድግምት አይነቶች

 ሁለት ዋና ዋና የድግምት አይነቶች ይገኛሉ፤

1. ሲህሩ አል-ተኸዩል
2. ሲህሩ አል-ሀቂቃህ

    1. ሲህሩ አል-ተኸዩል

     ድግምተኛው ሀይለኛ ማመሳሰያ ነገር ያዘጋጅና የተወሰነ የራሱን እንቅስቃሴ ያክልበታል፡፡ በዚህም ውስጥ ማመሳሰያዎችንና ለስራ የሚያስፈልገውን ቅርፃ ቅርፆችን ያስገባል፡፡ ከዚያም ይህን ተፅእኖ በሚያደርገው ውስጣዊ ሀይሉ ተጠቅሞ ለተመልካቾች የሚጨበጥ አስመስሎ ያወጣታል፡፡ ተመልካቾች በውጭ የምትታይ አድርገው ያስባሉ ነገር ግን ከሚያዩት ነገር በተጨባጭ ምንም የለም፡፡
 ይህን የድግምት ዓይነት ደጋሚው የሚጠቀመው በማመሳሰል ላይ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ሁለት አበይት ነገሮችን በመጠቀም ነው፡፡ በእነዚህ ሁለት ነገሮች አማካኝነት ድግምት የተሰራበት ግለሰብ ላይ የፈለገውን ያከናውናል፡፡ ማሳየት የፈለገውን ያሳየዋል፡፡
እነዚህ ሁለት አበይት ነገሮች፡-

1. በአይኖች ላይ መድገም
2. ማስፈራራት

   ለዚህም ነው አላህ  የፊርዓውን ደጋሚዎችን አስመልክቶ እንዲህ ያለው፡-
قَالَ أَلْقُوا ۖ فَلَمَّا أَلْقَوْا سَحَرُوا أَعْيُنَ النَّاسِ وَاسْتَرْهَبُوهُمْ وَجَاءُوا بِسِحْرٍ عَظِيمٍ [٧:١١٦]
«ጣሉ» አላቸው፡፡ (ገመዶቻቸውን) በጣሉም ጊዜ የሰዎቹን ዓይኖች ደገሙባቸው፡፡ አስፈራሩዋቸውም፡፡ ትልቅ ድግምትንም አመጡ፡፡›› (አል አዕራፍ 116)
 “ በሰዎች ዓይን ላይ ደገሙ”

ይህ ማለት የመጡበትን ማምታቻና ማታለያን በትክክለኛ እይታ እንዳይመለከቱባት ለወጧት ማለት ነው፡፡ “አስፈራሯቸውም” ማለትም በልቦቻቸው ውስጥ ፍራቻን አስገቡባቸው፡፡ እጅግ በጣም ማስፈራራትን አስፈራሯቸው፡፡ አደገኛ ማምታቻና እይታን መስለብ እንዲሁም በአይኖች ላይ ተፅእኖ ማድረግ በመሸፈንና በማደናበር ከማስፈራራት ጋር በሰው እይታ ላይ ተጽእኖ  ያሳድራል፡፡ የሰውዬዉ አመለካከት በደጋሚው ቁጥጥር ስር እስኪወድቅ ድረስ ማሳየት የሚፈለገውን ያሳየዋል፡፡ ሊያመሳስልበት የፈለገውን ያመሳስልበታል፡፡ ለዚህም ነው አላህ  እንዲህ ያለው፡-

 فَإِذَا حِبَالُهُمْ وَعِصِيُّهُمْ يُخَيَّلُ إِلَيْهِ مِن سِحْرِهِمْ أَنَّهَا تَسْعَىٰ  طه: ٦٦
‹‹ከድግምታቸው የተነሳ እነርሱ የሚሮጡ እባቦች ኾነው ወደእርሱ ተመለሱ፡፡››(ጣሃ 66)

አንቀጿ የምታመለክተው ለእነርሱ የታያቸው ማመሳሰያ የተከሰተው በድግምት መንገድ መሆኑን ነው፡፡
ሙሳ  ብትሩን በጣለው ጊዜ አላህ  በችሎታው የብትሩን ይዘት ለወጠው፡፡ ከእንጨት የተሰራች ብትር ከነበረችበት ወደ ትክክለኛ ህይወት ያላት ዘንዶ አድርጐ ፈጠራት፡፡ ምክንያቱም የነገሮች ሁሉ ፈጣሪ የሆነው በመለወጥ ላይም ቻይ ነው፡፡  ደጋሚዎቹ ይህን ባዩ ጊዜ ለአላህ  ተደፉ፣ ይህ ማመሳሰያ እንዳልሆነ በማወቃቸው፡፡ ምክንያቱም ድግምት በደጋሚዎች ላይ ተፅእኖ አያደርግም፡፡ የብትሩ መለወጥ የተከሰተው ሁሉም አእምሮአቸው እያስተዋለ ነው፡፡

 ስለዚህ ይህ ከባድ ክስተት መሆኑን አወቁ፡፡ ለአለህ በመደፋት ወደቁ፡፡ በሙሳና በሀሩን ጌታ አመንን አሉ፡፡ ስለዚህ ቁርአን ከነበሩት ግለሰቦች ሁሉ እነርሱ ብቻ የተደፉ መሆናቸውን ያወሳል፡፡

فَأُلْقِيَ السَّحَرَةُ سُجَّدًا قَالُوا آمَنَّا بِرَبِّ هَارُونَ وَمُوسَىٰ طه: ٧٠
ድግምተኞቹም ሰጋጆች ኾነው ወደቁ በሀሩንና በሙሳ ጌታ አመንን አሉ፡፡” (ጠሃ 7ዐ)

የዚህ አይነት ድግምት ብዙ አይነት ሲሆን ከጥንት ጊዜ ጀምሮ እስካለንበት ዘመን ድረስ ሲዘልቅ ቆይቷል፡፡ ከዚህ በፊት ስለነበረው የድግምት አይነት ለምሳሌ ያህል፡-

1. በሙሳ  እና በፊርዓውን ደጋሚዎች መሀከል የተካሄደ::

2. አንዳንድ ደጋሚዎች ብዙሃኑ ህብረተሰብን የሚያታልሉበት፣ ከሰዎች መሀከል ላምን ወይም ሴት ግመልን እንዲያቀርቡ ያዛሉ ሰዎችንም በዙሪያው ይሰበስባሉ ከዚያም ዓይኖቻቸው ላይ ይደግማሉ ከዚያም በላሟ ራስ ላይ ይቆማሉ፤ አንዳንዴም በፊንጢጣዋ ላይ ይቆማሉ፤ ከድግምቱ ተፅእኖ የተነሳ በአፏ በኩል ገብተው በፊንጢጣዋ በኩል መውጣታቸውን ያመሳስሉባቸዋል፡፡

3. በዘመናችን የዚህ አይነት ገፅታ ያለው “አስማት” ብለው የሚያከናውኑት የማምታታትና የማታለል ተግባር እንዲሁም አንዳንድ አላጋጮች በብዙሃኑ ህብረተሰብ ላይ የሚያመሳስሉት ተጠቃሽ ነው፡፡
ለምሳሌ፡- በአፉ ውሰጥ እንቁላል ጨምሮ በአይኑ ማውጣትን የመሰለ ወይም የተወሰነ ያህል ቁጥር ምላጭ በመዋጥ ከአፉ በክር የታሰሩ አድርጐ ማውጣትን የመሰለ ወይም አንድ ሴትን በሳጥን ውስጥ በማስገባት ከዚያም ሳጥኑን ብዙ ሰይፍ በመውጋት ይተከልበታል ከዚያም እርሷ ሰላማዊ ሆና ከሳጥኑ ውስጥ ትወጣለች፡፡

4. በዘመናችን ካሉ ሌላው የድግምት ዓይነት በሰዎች ዓይን ላይ በመድገም የሚሰሩት አንዳንድ አጭበርባሪዎች፣ በነጭ ወረቀት የተሞላ ሻንጣ ያመጣሉ ያ ድግምት የተሰራበት ግለሰብ እውነተኛ ብር መስሎት ይታየዋል፡፡ ከዚያም ደጋሚው ያሞኘዋል፡፡ አንድ መቶ ሺህ በአስር ሺህ ብቻ የሚቀይር ይላል፡፡ ይህ ሚስኪን በዚህ ይታለላል፡፡ እውነተኛ የሆነው አስር ሺህ ብር  ይሰጠውና የተጭበረበረ አንድ መቶ ሺህ ብር ይወስዳል፡፡ ይዞት ከሄደ ብዙ ሰአት ሳይቆይ የድግምቱ ተፅእኖ ይወገድለታል፡፡ አንድ መቶ ሺህ ምንም ጥቅም ወደ ሌለው ነጫማ ወረቆቶች ይለወጣሉ፡፡

5. ደጋሚዎች በአንዳንድ ግለሰቦች ላይ የድግምትን ተፅእኖ በማሳደር የሚፈፅሙት ተግባር ሲሆን ይኸውም በአስተሳሰባቸው ላይ ይሾሙባቸዋል፡፡ ለእነርሱም ታዣዦች ይሆናሉ፡፡ የተባሉትን ገንዘብ ታዛዦች ሲሆኑ ይሰጧቸዋል፡፡ የድግምቱ ተፅእኖ በተወገደ ጊዜ በእርግጥ ድግምት እንደተደረገበትና ገንዘቦቹም እንደተሰለቡበት ለተደገመበት ግለሰብ ይገለፅለታል፡፡ በዚህ ዘመን ከዚህም ሌላ ብዙ የተሰራጩና ብዙ ሰዎች የተታለሉበት የሆነ የድግምት አይነቶች አሉ፡፡

ፔጁን ላይክ ለማድረግ፡-
https://www.facebook.com/nosihr

ሼር በማድረግ ሙስሊሙን ዑማ በብዛት እየጎዳ ያለውን የሲህር በሽታ ለመከላከል የበኩሎን አስተዋፅዖ ያበርክቱ!

Comments