ድግምተኛ ሰይጣናትን ለመጥራትና ድግምትን ለመስራት የሚጠቀምባቸው መሰረተቢስ ፅሁፎችና ሰይጣናዊ
መጠበቂያዎች
ነብዩላህ ሱለይማን አላህን ከለመኑት በኃላ አንድም
ግለሰብ ጋኔንን (ጂንን) በቁጥጥር ስር ሊያውለው ወይም አገልጋይ ሊያደርገው አይችልም፡፡
ﮋ
ﮡ
ﮢ ﮣ ﮤ
ﮥ ﮦ ﮧ
ﮨ ﮩ ﮪ
ﮫ ﮬ ﮭ
ﮮ ﮯ ﮰ
ﮱ ﯓ ﯔ
ﯕ ﯖ ﯗﯘ
ﯙ ﯚ ﯛ
ﯜ ﯝ ﯞ
ﯟ ﯠ ﯡ
ﯢ ﯣ ﯤ
ﯥ ﮊ ص: 34 - 39
‹‹ሱለይማንንም በእርግጥ ፈተንነው፡፡ በመንበሩም ላይ አካልን ጣልን፡፡
ከዚያም በመጸጸት ተመለሰ፡፡ ጌታዬ ሆይ! ለእኔ ማር፡፡ ከእኔ በኋላ ለአንድም የማይገባንም ንግሥና ስጠኝ፡፡ አንተ ለጋሱ አንተ
ብቻ ነህና» አለ፡፡ ነፋስንም በትእዛዙ ወደፈለገበት ስፍራ ልዝብ ኾና የምትፈስ ስትኾን ገራንለት፡፡ ሰይጣናትንም
ገንቢዎችንና ሰጣሚዎችን ሁሉ (ገራንለት)፡፡ሌሎችንም በፍንጆች ተቆራኞችን (ገራንለት)፡፡ይህ ስጦታችን ነው::ያለ ግምት ለግስ ወይም
ጨብጥ አልነው::›› (ሷድ 34-39)
ነብያችን ﷺ
ከእለታት አንድ ቀን ለመስገድ
በቆሙበት “አዑዙ ቢላሂ ሚንከ” ማለትም “ከአንተ በአላህ እጠበቃለሁ” አሉ ከዚያም “አል አኑከ ቢለእነቲላሂ” ማለትም በአላህ እርግማን
እረግምሃለሁ” ሶስት ጊዜ ካሉ በኃላ የሆነ ነገር እንደሚቀበሉ እጃቸውን ዘረጉ፡፡ ሰላቱን በጨረሱ ጊዜ ሰሃባዎች እንዲህ ሲሉ ጠየቋቸው
“የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ከዚህ በፊት ሰምተንህ የማናውቀውን በሰላት ውስጥ የሆነ ነገር ስትል ሰማንህ እጅህንም ስትዘረጋ ተመለከትንህ”
አሏቸው እሳቸውም “የአላህ ጠላት ኢብሊስ የእሳት ችቦ በፊቴ ላይ ሊጥለው ይዞ መጣ ሶስት ጊዜ ከአንተ በአላህ እጠበቃለሁ አልኩኝ
ከዚያም ሊይዘው ፈለኩኝ፡፡ በአላህ እምላለው የወንድሜ ሱለይማን ፀሎት (ዱዓ) ባይኖር ኖሮ የታሰረ ሲሆን የመዲና ህፃናት ይጫወቱበት
ነበር፡፡” ሙስሊም ዘግበውታል
በቡኻሪና በሙስሊም እንደተዘገበው አቢ ሁረይራ ከነብያችን ﷺ እንዳወራው የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ “ሰይጣን ሰላቴን ለማቋረጥ በሀይለኛው ታገለኝና
አላህ ረድቶኝ አንቄ ያዝኩት እናንተ ታዩት ዘንድ በምሶሶ ላይ ላስረው አሰብኩኝና “ከእኔ በኃላ ለአንድም የማይገባንም ንግስና ስጠኝ”
የሚለውን የሱለይማንን ንግግር አስታወስኩኝ አላህ ሰይጣንን የተዋረደ ሲሆን መለሰው፡፡
እውነታው ይህ ከሆነ በደጋሚዎችና በሰይጣን መሀከል ያለው ግንኙነት ምስጢሩ ምን ይሆን? የጅን ሰይጣናት በመጥፎ ነገር ላይ
ደጋሚዎችን እንደሚያግዙ የታወቀ ነው፡፡ በመጥፎ ነገር ላይ ይታዘዟቸዋል ከጉዳያቸው የሚፈልጉትን ነገሮች ያስፈፅሙላቸዋል፡፡ ከሰይጣናት
ጋር ያላቸውን ግንኙነት ታላቁ ምሁር አልቃዲ በድሩ አልዲን አቢ አብደላህ መሐመድ ቢን አብደላህ አልሸበሊ አልሀነፊ “አካሙ አልመረጃን
ፊ አህካሚ አልጃን” በተባለው መፅሐፋቸው በአርባ ስምንተኛው ምዕራፍ ላይ ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፡- “ከሀዲያን ጂኖችና ሰይጣናት
ከህደትን በአላህ ላይ ማጋራትንና በአላህ ላይ ማመፅን ይመርጣሉ፡፡
ኢብሊስና ከሰይጣን የሆኑ ሰራዊቶቹ እርኩስ ተግባርን ይፈልጋሉ፡፡
ተንኮልንም ይሰሩበታል ያሳድዱታልም ተግባራቸው ለቅጣት የሚዳርጋቸው እና የሚያጠሙትንም አካል ለቅጣት ቢዳርገውም እርኩስ ነፍሶቻቸው
በምትፈልገው መሰረት በእነርሱ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡
ኢብሊስ እንዳለው፡-
ﮋ
قَالَ
فَبِعِزَّتِكَ لَأُغْوِيَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ () إِلَّا عِبَادَكَ مِنْهُمُ
الْمُخْلَصِينَ ﮊ ص: 82 - 83
“እርሱም አለ በአሸናፊነትህ ይሁንብኝ በመላ አሳስታቸዋለሁ ከእነርሱ
ምርጥ የኾኑ ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ” (ሷድ 82-83)
ﮋ ﮓ ﮔ ﮕ
ﮖ ﮗ ﮘ ﮙ ﮚ
ﮛ ﮜ ﮝ
ﮞ ﮟ ﮠ
ﮡ ﮢ ﮊ الإسراء: 62
‹‹እንዲህም አለ “ንገረኝ ይህ ያ በእኔ ላይ ያበለጥከው ነውን እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ብታቆየኝ
ዘሮቹን ጥቂቶች ሲቀሩ ወደ ስህተት በእርግጥ አስባቸዋለሁ አለ፡፡” (አል ኢስራእ 62)
አላህ እንዲህ አለ፡-
“ኢብሊስም በእነሱ ላይ ምኞቱን በእርግጥ ፈፀመ ከአመኑትም የኾኑት
ጭፍሮች በስተቀር ተከተሉት፡፡” (ሰባእ 2ዐ)
የሰው ልጅ ልቡ ወይም አእምሮው ከተበላሸ የሚጐዳውን ነገር መፈለግና በእርሱ መደሰት ይፈልጋል፡፡ እንደውም አእምሮውን፣
ሃይማኖቱን፣ ስነምግባሩን፣ አካሉንና ገንዘቡን የሚያበላሽ ነገርን በጣም ይናፍቃል፡፡ ሰይጣን እርኩስ መንፈስ ያለው ሲሆን የመድሃኒትና
የእጣ ባለቤት የሆነው ወደእርሱ ለመቃረብ የጅኖችን ስም በመፃፍና የሚወዱትን እንደክህደት፣ በአላህ ላይ ማጋራትን እንደጉቦ በመስጠት
ጉዳያቸውን እንዲፈፅሙላቸው ያደርጋሉ፡፡ ሊገደልለት የሚፈልገው ግለሰብ እንዲገደልለት ወይም በወንጀል ላይ እንዲተባበር አልያም አብሮ
እንዲሰራ ገንዘብን እንደሚሰጥ ግለሰብ፡፡
ስለዚህ አብዛኞቹ እነዚህ ነገራቶች የአላህን ንግግሮች በነጃሳ (በርክሰት) ነገር ይፅፋቸዋል፡፡
“ቁል ሁወላሁ አሀድ” የሚለውን አልያም ሌላ አንቀፆችን በነጃሳ (በርክሰት) ወይም በደም ወይም ከነጃሳ ውጪ በሆነ ነገር ነገር
ግን ሰይጣን በሚወደው ነገር ይፅፋሉ፡፡አልያም ሰይጣን በሚወደው ነገር ላይ ይናገራሉ:: ሰይጣን በሚወደው ነገር ከተናገሩ ወይም
ከፃፉ በፈለጉት አላማ ላይ ይረዳቸዋል፡፡ አልያም ከባህር በአንዱ ውስጥ እንዲሰምጡ ያደርጓቸዋል ወይም በአየር ላይ ራቅ ወዳለ ቦታ
ተሸክመው ይወስዷቸዋል አልያም ከሰው የሆነን ገንዘብ ይዘውላቸው ይመጣሉ፡፡
ከአጭበርባሪዎች ገንዘብ እና የአላህ ስም ያልተወሳበትን ሰይጣናት እንደሚሰርቁትና ሌሎች ነገራቶችንም ይዘውላቸው ይመጣሉ፡፡
ስለዚህ ያላቸው ግንኙነት በአላህ በመካድ ላይ የተገነባ ነው፡፡ ሰይጣናት ደጋሚዎች በአላህ ላይ እስካልካዱ ድረስ ፈፅሞ
አያገለግሏቸውም አይታዘዟቸውም፡፡ እንደሰይጣናት ፍላጐትና እንደደጋሚው አፈፃፀም በአላህ የመካዱ አይነት ይለያያል፡፡ አንዳንድ ጊዜ
የአላህን አንቀፆች በሽንትና በሰገራ (አላህ ይጠብቀንና) በመፃፍ አንዳንድ ጊዜ ቁርአኑን ከቀዳደዱ በኃላ በቆሻሻ ውስጥ ወይም በሽንት
ቤት በመጣል አንዳንድ ጊዜ ከአምስቱ የሰላት ወቅት ሱብሂ ወይም አስርን ለእነርሱ ድርሻ አድርጐ በመስገድ፣ አንዳንድ ጊዜ ሱጁድን
ለእነርሱ በማድረግና እነርሱን በማላቅ እንዲሁም ሌሎችንም የክህደት አይነት ይፈፅማሉ፡፡ ይህ ክህደት ከደጋሚው የሚከፈል ዋጋ መሆኑ ነው፡፡
አላህ እንደተናገረው፡-
ﮋ ﭪ ﭫ ﭬ
ﭭ ﭮ ﭯ ﭰ ﭱ
ﭲ ﭳ ﭴﭵ ﮊ
البقرة: 102
“እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም” (አል በቀራህ
1ዐ2)
ይህ አምልኮ የሚደረግለት ሰይጣን ከትላልቆቹ ሞገደኞች መሀከል ነው፡፡ ከደጋሚው ይህ አምልኮ ሲረጋገጥለት የድግምትን አፈፃፀምና
በሌላው ላይ እንዴት ተፅእኖ ማሳደር እንደሚችል ያስተምረዋል፡፡ አላህ እንዳለው፡-
ﮋ ﭙ ﭚ ﭛ
ﭜ ﭝ ﭞ
ﭟ ﭠ ﭡ ﮊ
البقرة: 102
“ሱለይማን አልካደም (ድግምተኛ አልነበረም) ግን ሰይጣናት ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ
ካዱ” (አል በቀራህ 1ዐ2)
ይህ ሁሉ ተግባራዊ የሚሆነው በመሰረተቢስ ፅሁፍና በሰይጣናዊ መጠበቂያ ሲሆን ደጋሚው ይህን ትምህርት ከትልቁ ሞገደኛው ይማርና በሰይጣናት ላይ ተፅእኖ
በማሳደር የድግምቱን ስራ ይፈፅማል::መሰረተ ቢስ የሆነው ፅሁፍና ሰይጣናዊ መጠበቂያ የተለያዩ አይነትና የተለያዩ ተግባራት ያላቸው
ሲሆን ከፍተኛ ተፅእኖ የማድረግ ሀይል አላቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከቁርአን አንቀፆች ጋር በማያያዝ ወይም “በስመላን” አልያም የአላህ
ስም ወይም የመላኢካዎችን ስም በመፃፍ ያገናኛሉ፡: ይህን የሚያደርጉት
1. ለማመሳሰልና ለማታለል ነው፡፡
2. በነዚህ በመታገዝ መሰረተቢስ በሆነው ፅሁፍና በሌሎች ስሞች
በእነዚያ ከሰይጣን በሆኑ በወዳጆቻቸው ስም የሽርክ ተግባራቸውን እውን ለማድረግ ነው፡፡
Comments
Post a Comment