በትክክለኛ ዘገባ የተወሩ መጠበቂያዎች፣ ሩቃና ጠቅላይ የዱዓ አይነቶች

በትክክለኛ ዘገባ የተወሩ መጠበቂያዎች፣ ሩቃና ጠቅላይ የዱዓ አይነቶች፡- 

1 “የሰዎች ጌታ የሆንከው አላህ ሆይ በሽታውን አስወግድልኝ ፣ አድነኝ አንተ አዳኝ ነህና፡፡ አንተ መድሃኒት ያደረገው ቢሆን እንጂ መድሃኒት የለም በሽታ የማያገኘውን መዳንን አድነኝ፡፡” አህመድ ዘግበውታል

2 “ሙሉ በሆነው በአላህ ንግግሮች እጠበቃለው ከሁሉም ሰይጣናትናከእኩይ ሰው ተንኰል እንዲሁም ከመጥፎ ዓይን ሁሉ በአላህ እጠበቃለሁ፡፡” የቡኻሪና የአህመድ ዘገባ

  3 “ከተፈጠረ ተንኮል ሁሉ ሙሉ በሆነው በአላህ ንግግሮች እጠበቃለሁኝ” የአህመድ ዘገባ

4 “ከአላህ ቁጣ፣ ከቅጣቱ፣ ከባሮቹ ተንኮል፣ ከሰይጣን ጉትጐታና ሰይጣን እኔን ከመቅረብ ሙሉ በሆነው በአላህ ንግግሮች እጠበቃለሁ” አህመድ ዘግበውታል

5 “መልካሙም ሆነ ክፉውን የማያመልጣቸውና ምሉዕ በሆኑት የአላህ ቃላት ከፈጠረው ፍጡር ክፋት ከሰማይ ከሚወርድ ክፉ ነገር ከምድር ላይ ከተፈጠረም ክፉ ነገር ከርሷ ከሚወጣም ክፉ ነገር በለሊትም በቀንም ከሚከሰት ፈታኝ የሆነ ክፉ ነገር ከክፉ የለሊት ጎብኝም በመልካም የሚጐበኝ ሲቀር እንጠበቃለን እጅግ በጣም ሩህሩህ የሆንከው አምላክ ሆይ ፀሎታችንን ተቀበለን”

 6 “በአላህ ስም አክምሃለሁ ከሚያስቸግርህ ነገር ሁሉ፣ ህይወት ካለው ተንኮል፣ ከምቀኛ አይን፣ አላህ ያድንህ፣ በአላህ ስም አክምሃለሁ” አህመድ ዘግበውታል

7 “አላህ ነፃ ያደርገሃል፣ ከሁሉም በሽታ ያድንሃል፣ ምቀኛ በተመቃኘ ጊዜ ከተንኮለኛ አይን ሁሉ፡፡” ሙስሊም ዘግበውታል

8 “በአላህ ስም አክምሃለው፣ ከሚያስቀጣህ ነገር ሁሉ፣ ከምቀኛ ምቀኝነት፣ ከአይን ባልተቤት ሁሉ አላህ ያድንህ” አህመድ ዘግበውታል

9 በሽተኛው እጁን በሚያመው ሰውነት ላይ ያደርጋውና እንዲህ ይላል “ቢስሚላህ” ሶስት ጊዜ ከዚያም “በአላህና በችሎታው ከሚሰማኝ ህመም እጠበቃለሁ” የሚለውን ሶስት ጊዜ ይላል፡፡




Comments